የዕለቱ የኢትዮዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች በመሸናነፍ ተጠናቅቀዋል።

0
175

ባሕር ዳር: የካቲት 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የ20ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ ተካሂደዋል። ኢትዮጵያ መድን ከወላይታ ድቻ በተገናኙበት ጨዋታ ወላይታ ድቻ በስድስተኛው ደቂቃ ጸጋዬ ብርሃኑ ባስቆጠራት ግብ አሸንፎ ወጥቷል።

በዚህ ጨዋታ የፕሪምየር ሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ልዩነቱን ከተከታዩ ሀድያ ሆሳህና የሚያሰፍለትን ሦስት ነጥብ ለመጣል ተገድዷል። ይሁን እንጅ አሁንም በ35 ነጥብ ፕሪምየር ሊጉን እየመራ ይገኛል።

12 ሰዓት ላይ በተካሄደው ሌላ ጨዋታ የአርባ ምንጭ ከተማ እና የፋሲል ከነማን ያገናኘ ጨዋታ ነበር። አርባ ምንጭ ከተማ በሁለተኛው ደቂቃ በታምራት ኢያሱ ግብ አሸንፎ መውጣት ችሏል። ፋሲል ከነማ ዛሬ ደረጃውን የሚያሻሽልበትን ዕድል አምክኗል።

የፕሪምየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዡን ኢትዮጵያ መድን፣ ሀድያ ሆሳህና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአንድ እስከ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ እየመሩ ይገኛሉ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here