ሊቨርፑል ኒውካስትል ዩናይትድን አሸንፎ መሪነቱን አጠናክሯል።

0
168

ባሕር ዳር: የካቲት 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ያደረገውን የሊግ መርሐ ግብር 2 ለ 0 በኾነ ውጤት አሸንፏል። የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች ማክ አሊስተር እና ዶምኒክ ስቦዝላይ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ማሸነፉን ተከትሎ ከተከታዩ አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ 13 ከፍ አድርጓል። መሐመድ ሳላህ በአንድ የውድድር ዓመት በሊጉ በርካታ ለግብ የኾነ ኳሶችን አመቻችቶ ያቀበለ በታሪክ ቀዳሚው ተጨዋች ለመኾን ተቃርቧል።

ሊቨርፑል የዛሬውን ጨዋታ ማሸነፉን ተከትሎ በ67 ነጥቦች የደረጃ ሰንጠረዡን ይመራል።

በታዘብ አራጋው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here