ባሕር ዳር: የካቲት 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ያደረጉት የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። በቀጣይ አመት በሞሮኮ አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ከዩጋንዳ ያደረገው ቡድኑ በመለያ ምት አሸንፏል።
ዛሬ ዘጠኝ ሰአት ላይ በአበበ ቢቂላ ስቴዲየም በተደረገው የመልስ ጨዋታ ሉሲዎቹ 2 ለ 0 አሸንፈዋል። በሁለተኛው አጋማሽ የዩጋንዳዋ አጥቂ በሁለት ቢጫ ካርድ ከሜዳ በወጣችበት ጨዋታ አረጋሽ ካልሳ 66ኛው እና ተቀይራ የገባቸው እጸገነት ግርማ 96ኛው ደቂቃ ላይ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ሉሲዎቹ በዛሬው የመልስ ጨዋታ ቢያሸንፉም ካምፓላ ላይ ባደረጉት የመጀመርያ ጨዋታ 2 ለ 0 መሸነፋቸውን ተከትሎ በድምር ውጤት አቻ በመኾናቸው ወደ መለያ ምት አምርተዋል። አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠው መለያ ምት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 5 ለ 4 በማሸነፍ ወደ ሁለተኛው ዙር ማጣሪያ አልፏል።
ብሔራዊ ቡድኑ ከ12 ዓታትመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለመመለስ በመጨረሻው ማጣሪያ ከኢኳቶሪያል ጊኒ እና ታንዛንያ አሸናፊ የሚገናኝ ይሆናል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!