በፕሪምየር ሊጉ ዛሬ ወሳኝ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

0
146

ባሕር ዳር: የካቲት 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በ27ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ አምስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። ምሽት 4 ሰዓት ተኩል በሊጉ 26 ጨዋታዎችን አድርጎ 37 ነጥብ በመያዝ 11ኛ ላይ የተቀመጠው ብሬንትፎርድ በ31 ነጥብ 14ኛ ላይ የሚገኘውን ኤቨርተንን ይጋብዛል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በቅርብ በተገናኙባቸው አምስት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ኤቨርተን በሦስቱ አሸንፎ እና በሁለቱ አቻ በመለያየት የበላይ ነው፡፡ በሌላ ጨዋታ 30 ነጥብ በመያዝ 15ኛ ላይ የሚገኘው ማንቸስተር ዩናይትድ ወራጅ ቀጣና ውስጥ ከሚገኘው ኢፕስዊች ታውን ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ይጫወታል፡፡
ኢፕስዊች ጨዋታውን ቢያሸንፍም ከወራጅ ቀጣናው መውጣት አይችልም፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ከ30 አምስተኛ ደረጃ የሚገኘው ማንቸስተር ሲቲ ከሜዳው ውጭ13ኛ ላይ ከተቀመጠው ቶትንሃም ጋር ይጫወታል፡፡ ጨዋታውን ያሸነፈው ቡድን ደረጃውን ያሻሽላል፡፡ በደረጃ ሰንጠረዡ ሦስተኛ ላይ የሚገኘው ኖቲንግሃም ፎረስት ደግሞ በሁለተኛነት የተቀመጠው አርሰናልን የሚጋብዝበት ጨዋታ ተጠባቂ ነው። ጨዋታው ምሽት 4 ሰዓት ከ30 ይካሄዳል፡፡

ኖቲንግሃም ፎረስት በአርሰናል ከተሸነፈ እና ማንቸስተር ሲቲ ማሸነፍ ከቻለ በግብ ክፍያ በልጦ የሦስተኛነት ደረጃን የሚረከብ ይኾናል፡፡ ሊቨርፑል ከኒውካስትል ዩናይትድ ምሽት 5 ሰዓት 15 በአንፊልድ የሚያደርጉት ጨዋታም ይጠበቃል፡፡ ሊቨርፑል ይበልጥ መሪነቱን ለማጠናከር ኒውካስትል ዩናይትድ ደግሞ የቀጣይ ዓመት የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎን ለማግኘት ስለሚጫወቱ ጨዋታው አጓጊ ነው፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በቅርብ በተገናኙባቸው አምስት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ሊቨርፑል በአራቱ ድል በመንሳት እና በአንዱ ደግሞ አቻ በመለያት የበላይነትን ይዟል፡፡ ሊጉን ሊቨርፑል ሲመራው አርሰናል ይከተላል፤ ኖቲንግሃም ፎረስት ደግሞ ሦስተኛ ነው፡፡ ኢፕስዊች ታወን፣ሌስተር ሲቲ እና ሳውዝአምፕተን ወራጅ ቀጣናው ላይ ተቀምጠዋል ሲል ቢቢሲ ስፖርት በድረ ገጹ አስነብቧል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here