በእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ የ27ተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ይጀመራሉ።

0
140

ባሕር ዳር: የካቲት 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሊቨርፑልን ባለክብር ሊያደርግ ተቃርቧል እየተባለለት ያለው የእንግሊዝ ፕሪምየርሊግ ምሽት አራት ጨዋታዎችን ያከናወናል። ከዛሬ መርሐ ግብሮች መካከል ብራይተን ከበርንማውዝ የሚገናኙበት መርሐ ግብር የተሻለ ግምት አግኝቷል። ሁለቱ ክለቦች በሦሥት ነጥብ ተለያይተው የአውሮፖ መድረክ ተሳትፎ ለመግኘት እየተፎካከሩ ነው።

በርንማውዝ በ43 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ብራይተን ደግሞ በ40 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በሌሎች ጨዋታዎች ደግሞ ቼልሲ ከሳውዝአፕተን፣ ክርስቲያል ፓላስ ከአስቶንቪላ እና ወልቭስ ከፉልሃም ይጫወታሉ። ፕሪምየርሊጉን ሊቨርፑል በ64 ነጥብ እየመራ ነው። አርሰናል በ53 ነጥብ ይከተላል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here