የ30 ኪሎ ሜትር የብስክሌት የፍፃሜ ውድድር በሁመራ ከተማ ተካሄደ፡፡

0
154

ሁመራ: የካቲት 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን እየተካሄደ በሚገኘው በዞኑ መላው ስፖርት ውድድር በ30 ኪሎ ሜትር የወንዶች የከተማ የብስክሌት ውድድር በሁመራ ከተማ ተካሂዷል። በፍፃሜ ውድድሩም የዳንሻ ከተማ አሥተዳደር ብስክሌተኛ ገዘሃይ ካልአዮ በአንደኝነት አጠናቅቋል።

የሰቲት ሁመራ ከተማ አሥተዳደር ተወዳዳሪዎች ፊልሞን ምሕረትዓብ እና ሳሙኤል የማነ 2ኛ እና 3ኛ በመኾን ተከታትለው ገብተዋል።

በ11 ተወዳዳሪዎች እና በሁለት ክለቦች በተካሄደው በዚህ ውድድር ጠንካራ ፉክክር ነው የተደረገው።

የከተማ ውድድሩ መጠናቀቁን ተከትሎ የበርሃ ውድድር በቀጣይ ቀናት የሚካሄድ መኾኑን ከአዘጋጆች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የዞኑ መላው ስፖርታዊ ውድድር በጠንካራ ፉክክሮች መካሄዱንም እንደቀጠለ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here