ፋሲል ከነማን በገቢ ማጠናከር ዓላማ ያደረገ ሩጫ በሁመራ ከተማ ተካሄደ።

0
204

ሁመራ: የካቲት 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን “ንግሥና እንደ ፋሲል ከፍታ እንደ ዳሽን” በሚል መሪ መልዕክት ስድስተኛው የፋሲል ከነማ ሩጫ በሁመራ ከተማ ተካሂዳል።

ሩጫው በአዋቂ ሴቶች፣ በአዋቂ ወንዶች እና በሕጻናት ተከፋፍሎ ነው የተካሄደው። በሩጫው ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ለወጡ ተወዳዳሪዎች የሜዳልያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ።

ሁለተኛው የመላው ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ዘመናዊ የስፖርት ውድድር ዛሬ የሚጀምር ሲኾን የፋሲል ከነማ ሩጫም የውድድሩ መክፈቻ ኾኗል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here