ባሕር ዳር: የካቲት 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሳዑዲው አልናስር እግር ኳስ ቡድን ሮናልዶን በዓመት 200 ሚሊዮን ዩሮ በመክፈል ለሁለት ዓመት ተኩል በሚቆይ ኮንትራት ያስፈረመው እንደ አውሮፖውያን አቆጣጠር 2022 መጨረሻ ላይ ነበር። ተጫዋቹም ለአል ናስር በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች ድንቅ ብቃቱን በማሳየት ተመልካቾችን ከመቀመጫቸው አስነስቶ አስጨብጭቧል።
በ90 ጨዋታዎችም ተሰልፎ 82 ግቦችን አስቆጥሯል። 19 ለግብ የሚኾኑ ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል ውጤታማ ተጫዋች ነው። ስፖርትስ ሬሽን በድረ ገጹ እንዳስነበበው የፖርቱጋላዊው ኮከብ ሮናልዶ ውሉ የሚጠናቀቅበት ሰኔ 2025 በመቃረቡ ክለቡ የተጫዋቹን ለማቆየት ድርድር ላይ ቆይቷል።
በዚህም ተጫዋቹ ከአልናስር ጋር እስከ ሰኔ 2026 ለመቆየት ተስማምቷል። የቀድሞው የእንግሊዙ ማንቸስተር ዩናይትድ፣ የስፔኑ ሪያል ማድሪድ እና የጣሊያኑ ጁቬንቱስ ኮከብ እንዲኹም የአምስት ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊው ሮናልዶ የእግር ኳስ ሕይዎቱን በአልናስር ለመጨረስ ፍላጎት እንዳለውም ተናግሯል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!



