በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ማንቸስተር ሲቲ ከሪያል ማድሪድ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

0
224

ባሕር ዳር: የካቲት 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአውሮፖ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ። ማንቸስተር ሲቲ እና ሪያል ማድሪድ የሚያደርጉት ጨዋታ ደግሞ በጉጉት ይጠበቃል።

ሁለቱ ክለቦች ዛሬ ምሽት ሲገናኙ ባለፉት አራት የውድድር ጊዜያት ለአራተኛ ጊዜ ይኾናል። ወደ ጥሎ ማለፉ ድልድል ለመግባት የሚያደርጉት የዛሬው ጨዋታ ትኩረት ስቧል።

ማንቸስተር ሲቲ እና ሪያል ማድሪድ በአዲስ የውድድር ስልት እየተካሄ በሚገኘው የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ያሳዩት አቋም ያልተጠበቀ ነው።

ሁለቱ ቡድኖች እስካሁን 15 ጊዜ ሲገናኙ እያንዳንዳቸው 5ጊዜ አሸንፈዋል 5ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል። ጨዋታውም 5:00 ይካሄዳል።

በሌሎች ጨዋታዎች ብሬስት ከፒኤስጅ 2 ፡45 ይገናኛሉ። ጁቬንቱስ ከፒኤስቪ እና ስፖርቲንግ ሊዝበን ከ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ የሚያደርጉት ጨዋታ ምሽት 5:00 ይካሄዳል።

በምሥጋናው ብርሃኔ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCor

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here