አዲስ አበባ: የካቲት 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ለሁለት ቀናት በሚካሄደው መድረክ በዋናነት ሥስት ሰነዶች ቀርበው ምክክር እና ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሏል።
የአካዳሚውን የ10 ዓመት የተልዕኮ ውጤታማነት ውይይት እንደሚደረግበት ተመላክቷል። የሠልጣኞች የውጤታማነት ፋይዳ ፣ የኢትዮጵያ ስፖርት መሠረታዊ ፅንሰ ሐሳብ እና የመሪዎች ሚና የሚሉ ሰነዶችም ቀርበው ምክክር እና ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሏል።
በውይይት መድረኩ የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ የማኅበራዊ ልማት፣ የባሕል እና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወርቅሰሙ ማሞ፣ የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ዳይሬክተር አምበሳው እንየው እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
“ለሀገራችን የስፖርት እድገት የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ሚና የላቀ ነው” በሚል መሪ መልዕክት የሚካሄደው የባለድርሻ አካላት ምክክር ከዛሬ የካቲት 03/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!