ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ መድን ጋር ዛሬ ይጫወታል።

0
145

ባሕር ዳር: ጥር 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ 18ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቀጥለው ይካሄዳሉ።

የኢትዮጵያ ፕሪምዬር ሊግ 18ኛ ሳምንት በዛሬ መርሐ ግብሩ ሁለት ጨወታዎች ይደረጋሉ። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሀዋሳ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ ደግሞ የዕለቱ ቀዳሚ ጨዋታ ነው። ጨዋታው ቀን 9:00 ይካሄዳል። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ18 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ሀዋሳ ከተማ በ15 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ነው።

የዕለቱ ሁለተኛው ጨዋታ ፋሲል ከነማን ከኢትዮጵያ መድን ጋር ያገናኛል። በጥሩ ብቃት ላይ የሚገኘው ኢትዮጵያ መድን እና በደካማ አቋም ላይ የሚገኘው ፋሲል ከነማ የሚያደርጉት ጨዋታ ምሽት 12: 00 ይካሄዳል።

ፋሲል ከነማ ባለፉት አምስት ጨዋታዎች በአንድ ጨዋታ ተሸንፎ፣ በሦስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል። አንደኛውን ጨዋታ ደግሞ አሸንፏል። በ17ኛ ሳምንት ድሬዳዋ ከተማን ያሸነፈው ፋሲል ከነማ ዛሬ ከሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል።

ኢትዮጵያ መድን በ32 ነጥብ ፕሪምዬር ሊጉን እየመራ ነው። 20 ነጥቦችን የሰበሰበው ፋሲል ከነማ ደግሞ 13ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ፋሲል ከነማ ዛሬ ድል የሚቀናው ከኾነ ደረጃውን ያሻሽላል። ኢትዮጵያ መድን ድል የሚቀናው ከኾነ ደግሞ መሪነቱን ያጠናክራል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here