ባሕር ዳር: ጥር 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የ27 ዓመቱ ዩናይትድ አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድ አስቶንቪላን በውሰት ተቀላቅሏል።
የዩናይትድ ምንጮች እንዳሉት በውሉ መሰረት አስቶን ቪላ 75 በመቶ የራሽፎርድ ደሞዝ ይሸፍናል።
ራሽፎርድ በኢንስታግራም ገጹ “ይህ ውል እንዲፈጸም በማድረጋቸው ማንቸስተር ዩናይትድን እና አስቶንቪላን ማመስገን እፈልጋለሁ” ብሏል።
“በቀሪው የውድድር ዘመን ለማንቸስተር ዩናይትድ መልካሙን ሁሉ እመኛለሁ” ነው ያለው፡፡
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የተጫዋቾች ዝውውር ዛሬ ሌሊት ይጠናቀቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!