አጫጭር የዝውውር መረጃዎች።

0
238

ባሕር ዳር: ጥር 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አርሰናል የ29 ዓመቱን እንግሊዛዊ አጥቂ ኦሊ ዋትኪንስን ለማስፈረም አሁንም ሙከራ እያደረገ ስለመኾኑ ነው የተገለጸው። ማንቸስተር ዩናይትድ እንግሊዛዊ አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድን በውሰት ለመስጠት ከባርሴሎና ጋር ድርድር ላይ ነው። አሁን ባለው ኹኔታ ግን እስከ ዝውውሩ ማጠናቀቂያ ወቅት ላያጠናቅቁ ይችላሉ ሲል ዘቴሌግራፍ አስነብቧል።

አርሰናል የጥር የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት የፈረንሳይን አጥቂ ማቲስ ቴል ለማዘዋወር ጥረት እያደረገም ይገኛል። ስቲቨን ጄራርድ ከ18 ወራት በኋላ የሳውዲ ፕሮ ሊግ ክለብ የኾነውን አል ኢቲፋክን ለመልቀቅ ተቃርቧል። ቼልሲ የ22 ዓመቱን ጣሊያናዊ አማካይ ሴሳሬ ካሳዴይን ለቶሪኖ ለመልቀቅ እየተነጋገረ ሲኾን የተጫዋቹ ሌላኛው ፈላጊ ላዚዮ አሁን ላይ ከውድድሩ ውጪ ኾኗል ነው የተባለው።

የጀርመን ክለቦች ባየር ሙኒክ እና ቦሩሲያ ዶርትሙንድ የእንግሊዝን የክንፍ ተጫዋች ታይለር ዲቢሊንግን ለማስፈረም ከቶተንሃምጋር ፉክክር ውስጥ መግባታቸውን ዘሰን አስነብቧል። የኮሎምቢያ አጥቂ ጆን ዱራን በ77 ሚሊዮን ዩሮ ከአስቶንቪላ ወደ አል ናስር ከመዘዋወሩ በፊት በለንደን የሕክምና ምርመራ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ቶተንሃም በዚህ የዝውውር ጊዜ ቴልን በውሰት የማስፈረም ፍላጎት ስለመኖሩ ተነግሯል። ናፖሊ የናይጄሪያዊውን አጥቂ ቪክቶር ኦሲምሄን የውሰት ዝውውር ቋሚ ለማድረግ ጋላታሳራይ ያቀረበውን የ65 ሚሊዮን ዩሮ ውድቅ አድርጓል።

ኒውካስትል ዩናይትድ የአየርላንድ ሪፐብሊክ የክንፍ ተጫዋች ካይል ፍዝጌራልድን ለማስፈረም የሚያስችል ሁኔታ ላይ ስለመኖሩ ነው ኢንሳይደር የዘገበው።

ናፖሊ አርጀንቲናዊውን የክንፍ ተጫዋች አሌሃንድሮ ጋርናቾን ለማዘዋወር ማንቸስተር ዩናይትድ ያቀረበውን ጥያቄ መልሶ ሊያይ ይገባል ማለቱን ፋብሪዚያኖ ሮማኖ ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ አስነብቧል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here