የአውሮፖ ሻምፒዮንስ ሊግ ተጠባቂ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ።

0
162

ባሕር ዳር: ጥር 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ በአዲስ የውድድር ስልት ውድድሩን እያካሄደ ነው። በውድድሩ 36 ቡድኖች እየተሳተፉ ነው። ክለቦች ወደ ጥሎ ማለፉ ለመቀላቀል ዛሬ የመጨረሻ ጨዋታዎችን ያደርጋሉ።

በደረጃ ሠንጠረዡ ከአንድ እስከ ስምንት ይዘው የሚያጠናቅቁ ክለቦች በቀጥታ 16ቱን ይቀላቀላሉ። በሰንጠረዡ ከ9 እስከ 24 ኾነው የሚያጠናቅቁ ክለቦች ደግሞ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ያደርጋሉ።

እስካሁን በተካሄዱ ሰባት ጨዋታዎች ሊቨርፑል እና ባርሴሎና ብቻ በቀጥታ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። አርሰናል፣ ኢንተር ሚላን፣ አትሌቲኮ ማድሪድ እና ሌሎች በደረጃ ሰንጠረዡ እስከ ስምንተኛ የሚገኙ ክለቦች በቀጥታ የማለፍ ዕድላቸውን የሌሎችን ውጤት ሳይጠብቁ በራሳቸው ይወስናሉ።

በአንጻሩ ማንቸስተር ሲቲ እና ፒኤስጅ ከውድድሩ የመውጣት ትልቅ ስጋት ላይ ኾነው የዛሬውን ጨዋታ ያደርጋሉ። በተለይ የማንቸስተር ሲቲ በስምንት ነጥብ 25ኛ ደረጃ ላይ መገኘቱ ለጋርድዮላ እና ደጋፊዎቹ ጭንቀት ፈጥሯል።

ዛሬ ሁሉም ጨዋታዎች በተመሳሳይ 5:00 ይካሄዳሉ። ማንቸስተር ሲቲ ከክለብ ብራግ፣ ስቱትጋርት ከፒኤስጅ የሚገናኙባቸው ጨዋታዎች ደግሞ ወሳኝ ተብለዋል።

ባርሴሎና ከአታላንታ፣ ብረስት ከሪያል ማድሪድ፣ ጁቬንቱስ ከቤኔፊካ፣ ኢንተርሚላን ከሞናኮ፣ ጅሮና ከአርሰናልም ጥሩ ፉክክር ሊታይባቸው እንደሚችል ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here