ባሕር ዳር: ጥር 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አርሰናል እና ቶተንሃም ለ22 ዓመቱ የአትሌቲክ ቢልባኦ እና የስፔን የክንፍ ተጫዋች ኒኮ ዊሊያምስ የውል ማፍረሻ 48 ነጥብ 5 ሚሊዮን ፓውንድ ለመክፈል ፈቃደኛ እንደኾኑ የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ። አርሰናል የ18 ዓመቱን የኖርዌይን አማካኝ ስቬር ኒፓንን ለማስፈረም ጥረት እያደረገ መኾኑም ታውቋል።
የማንቸስተር ሲቲ ንብረት የኾነውን ጀምስ ማክቴን በውሰት ለማዘዋወር ባየር ሊቨርኩሰን እየተደራደረ ስለመኾኑ ዴይሊ ሜል አገኘውት ያለውን መረጃ አስነብቧል። አስቶንቪላ ከየቼልሲው ተከላካይ አክስኤል ዲሳሲ ጋር በግል መስማማቱን ፋቭሪዚዎ ሮማኖ አስነብቧል።
የቼልሲን አጥቂ ጆአዎ ፊሊክስ አስቶንቪላን መቀላቀል እንደሚፈልግ ቶክ ስፖርት ዘግቧል። ሊቨርፑል እና ቼልሲ የቦርሲያ ዶርትመንድን አጥቂ ካሪም አዴይሚ ለማስፈረም ከናፖሊ ጋር እየተፎካክሩ መኾኑ ታውቋል። ማንቸስተር ዩናይትድ ማርከስ ራሽፎርድ ክለቡን የሚለቅ ከሆነ የቼልሲ አጥቂ ክሪስቶፈር ንኩንኩን በውሰት ሊያዘዋውሩ ይችላሉ እየተባለ ነው።
ቼልሲ የአርቢ ላይፕዚግ የፊት መስመር ተጫዋች ቤንጃሚን ሴስኮ እና የባየር ሙኒክ አጥቂ ማቲስ ቴልን ለማስፈረም እያሰቡ ነው ብሏል ቲም ቶክ በዘገባው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!