ባሕር ዳር: ጥር 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ነይማር በውድ ዋጋ ወደ ሳዑዲው ክለብ አል ሂላል ወዛወሩ ይታወሳል። ነገር ግን ተጫዋቹ በጉዳት ምክኒያት ክለቡን ማገልገል አልቻለም።
ከፈረንሳዩ ፒኤስጅ ወደ አል ሂላል ከተዛወረ ሁለት ዓመታት ተቆጥረዋል። ነገር ግን በእነዚህ ጊዚያት የክለቡን መለያ ለብሶ የተጫወተው ሰባት ጊዜ ብቻ ነው። ያስቆጠረው ግብም አንድ ነው።
ለነይማር ዝውውር 94 ሚሊየን ዩሮ የከፈለው አል ሂላል የብራዚላዊን ብቃት ሳያገኝ አሁን በስምምነት ከተጫዋቹ ጋር መለያየቱን አሳውቋል።
የተጫዋቹ ቀጣይ ክለብ የብራዚሉ ሳንቶስ ሊኾን እንደሚችል እየተወራ ነው። ሳንቶስ የነይማር የልጅነት ክለቡም ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!