ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ናኦሚ ግርማ በዓለም ሪከርድ ዋጋ ለቸልሲ ፈርማለች።

0
196

ባሕር ዳር: ጥር 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ቼልሲ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ናኦሚ ግርማን በሴቶች የዓለም ሪከርድ ዋጋ ነው ማስፈረሙ እና ንብረቱ ማድረጉ የተዘገበው። ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ናኦሚ ግርማ በአሜሪካ የሴቶች እግርኳስ ጨዋታ ላይ ዕውቅና ካገኙ እና ችሎታቸውን በሥራ ከገለጹ የተከላካይ መስመር ተጫዋቾች መካከል ትጠቀሳለች።

ተጫዋቿ በሴቶች የዓለም ሪከርድ ዋጋ ከሳንዲያጎ ዌቭ ዝውውሯን ካጠናቀቀች በኋላ ቼልሲን መቀላቀሏን ቢቢሲ አስነብቧል። የ24 ዓመቷ ወጣት ናኦሚ ግርማን በዚህ ሳምንት ለሳንዲያጎ 900 ሺህ ዩሮ የከፈለው ቸልሲ ተጫዋቿን እንደ አውሮፖውያኑ አቆጣጠር እስከ 2029 ድረስ ለማቆየት ነው ውል የተፈራረመው።

ተጫዋቿ በሰጠችው አስተያየት እንዳለችው “እዚህ በመሆኔ በጣም ደስተኛ ነኝ እናም በተሎ ለመጫዎት ጓጉቻለሁ” ብላለች። ወደ ቼልሲ እንድመጣ ያደረጉኝ ብዙ ነገሮች አሉ የምትለው ተጫዋቿ ባሕሉ፣ የአሸናፊነት አስተሳሰቡ፣ ሠራተኞች እና ተጫዋቾች ምርጫዋ እንደኾኑም ነው ያረጋገጠችው።

ለመማር እና ለማደግ ጥሩ ቦታ ስለመኾኑ ገልጻ ማድረግ እንደምትፈልግ እና ለዚህም ይህ ትክክለኛ ምርጫ እንደኾነ እንደሚሰማት ነው ያብራራችው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here