ጎንደር: ጥር 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ዩኒቨርስቲ የምሥረታ በዓሉን በተለያዩ ዝግጅቶች እያከበረ ነው። በዓሉ ከጥር 14/2017 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ድረስ 20 በሚኾኑ ሁነቶች ይከበራል።
የጎንደር ዩኒቨርስቲ 70ኛ ዓመት እና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 100ኛ ዓመት የምሥረታ በዓልን ነው በተለያዩ ዝግጅቶች የሚያከብረው።
የመርሐ ግብሩ አንድ አካል የኾነው ውድድር እየተካሄደ ነው። አትሌቶች፣ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ፣ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በውድድሩ ተሳትፈዋል።
የሩጫ ውድድሩ መነሻውን ከቸቸላ ሆስፒታል አድርጎ መድረሻው ቴዎድሮስ ግቢ ስታዲየም ይሆናል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!