ባሕር ዳር: ጥር 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ማንቸስተር ዩናይትድ የግራ መስመር ተከላካዩን ፓትሪክ ዶርጉን ለማስፈረም ጥረት እየተደረገ ስለመኾኑ ተዘግቧል። ዩናይትዶች የ23 ዓመቱ የዎልቭስ የግራ መስመር ተከላካይ ራያን አይ ኑሪን፣ ከክሪስታል ፓላስ የግራ መስመር ተከላካይ ቲሪክ ሚቼልን፣ ከፓሪስ-ሴንት ዠርሜን ኑኖ ሜንዴዝ ለማስፈረም የሚያደርጉት ጥረትም እንደቀጠለ ነው።
የማንቸስተር ዩናይትድ ንብረት የኾነውን አሌሃንድሮ ጋርናቾን ለማስፈረም ናፖሊ ጥረት እያደረገ ነው። አርጀንቲናዊውን ተጫዋች ናፖሊ ለማስፈረም 50 ሚሊዮን ፓውንድ ስለማቅረቡም አየተነገረ ነው።
የአስቶንቪላው ጆን ዱራን ዌስትሃም ለመውሰድ 57 ሚሊዮን ፖውንድ የዝውውር ሂሳብ ቢያቀርብም በአስቶንቪላ በኩል ጥያቄው ውድቅ ስለመደረጉ ዘቴሌግራፍ አስነብቧል።
ቼልሲ ፖርቱጋላዊ ተከላካይ ሬናቶ ቬጋን በመሸጥ የጁቬንቱሱ አጥቂ ዱሳን ቭላሆቪች ለማዛወር ከጣሊያኑ ክለብ ጋር እየተነጋገረ ስለመኾኑ የጣሊያን የመገናኛ ብዙኀን እየዘገቡ ይገኛሉ።
የሪያል ማድሪድ አሠልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ በክረምቱ ክለቡን ሊለቁ መኾኑ ሲነገር ጣልያናዊውን አሠልጣኝ ለመተካት የባየር ሊቨርኩሰን አሠልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ተመራጭ ኾነው መገኘታቸውን የእንግሊዝ ጋዜጦች አስነብበዋል።
የ29 ዓመቱ የማንቸስተር ሲቲ አማካይ ጃክ ግሬሊሽ በኢንተር ሚላን እና በቦሩሲያ ዶርትሙንድ እየተፈለገ ቢኾንም ተጫዋቹ በኢትሃድ የመቆየት እድሉ ሰፊ ስለመኾኑ ነው የተነገረው።
የ33 ዓመቱ ቤልጄየማዊ አማካይ ኬቨን ደብሩይና ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ያለው ውል እያለቀ ቢኾንም ውሉ እስካሁን እንዳልታደሰ ነው የተገለጸው።
ቶተንሃሞች የኢፕስዊች ታውንን አጥቂ ሊያም ዴላፕን በዚህ ወር ለማስፈረም እያሰቡ ቢኾንም ቼልሲ ተጫዋቹን የሚፈልገው በመኾኑ ከፍተኛ ፉክክር ሊገጥማቸው ይችላል ነው የተባለው።
ኤሲ ሚላን የማንቸስተር ዩናይትዱን ዴንማርካዊ ኢንተርናሽናል አጥቂ ራስሙስ ሆይሉንድን እና የ23 ዓመቱን ሆላንዳዊ አጥቂ ጆሹዋ ዚርክዚን በውሰት ለመውሰድ እንዳሰበ ተዘግቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!