ዛሬ ፋሲል ከነማ ከመቻል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

0
141

ባሕር ዳር: ጥር 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በ15ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ከመቻል ጋር ዛሬ ይጫወታል። ፋሲል ከነማ በ16 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። መቻል ደግሞ በ25 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ይገኛል።

ፋሲል ከነማ ባለፍት ሳምንታት ካደረጋቸው ሦስት ጨዋታዎች መካከል ሁለቱን አቻ ሲለያይ አንዱን ደግሞ ተሸንፏል። በሌላ በኩል ተጋጣሚው መቻልም አንዱን አሸንፎ ሌላውን አቻ ሲወጣ አንዱን ደግሞ ተሸንፏል። በዚህም ሁለቱ ክለቦች የሚያደርጉት ጨዋታ ተመጣጣኝ ይኾናል ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል ደርሶ ግብ ማስቆጠር ላይም ቢኾን ሁለቱም ክለቦች ደካማ የሚባሉ ናቸው። ባለፉት ሦስት ጨዋታዎች የተጋጣሚያቸውን መረብ መድፈር የቻሉበት ጊዜ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። ሁለቱ ክለቦች እስካሁን 12 ጊዜ የመገናኘት ዕድል ነበራቸው በዚህም ስድስት ጊዜ ፋሲል ከነማ ማሸነፍ ሲችል ሦስቱን ደግሞ መቻል አሸንፏል።

በሦስት ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል። ጨዋታቸውም ምሽት 12 ሰዓት ላይ ይካሄዳል፡፡ በ15ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሌላው የሚጠበቀው ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ እና በወልዋሎ አዲግራት በኩል የሚካሄደው ነው፡፡ ጨዋታውም 9 ሰዓት ላይ ይካሄዳል፡፡

የደረጃ ሠንጠረዡን በ26 ነጥብ የኢትዮጵያ መድኅን ሲመራ ሀዲያ ሆሳዕና በግብ ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ ነው። መቻል በ25 ነጥብ ሦስተኛ በመኾን ይከተላሉ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here