በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ የባሕር ዳር ከተማ እና የኢትዮጵያ መድን ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡

0
162

ባሕር ዳር: ጥር 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በ15ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማን ከኢትዮጵያ መድኅን ጋር ያገናኛል፡፡

በ22 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ የሚገኘው ባሕር ዳር ከተማ በ23 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ከሚገኘው የኢትዮጵያ መድኅን ጋር ነው ጨዋታቸውን የሚያደርጉት
በዛሬው ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማ እንደሚፈተን ይጠበቃል፡፡ በተለይም ባሕር ዳር ከተማ በተከታታይ ካደረጋቸው ሦስት ጨዋታዎች ውስጥ ሁለቱን ጨዋታዎች አቻ ሲለያይ አንዱን ጨዋታ ነው ማሸነፍ የቻለው፡፡

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መድኅን አሁን ያለው አቋም ጠንካራ የሚባል ነው። በተከታታይ ካደረጋቸው ሦስት ጨዋታዎች ሁሉንም ማሸነፉ የዛሬውን ጨዋታ ተጠባቂ አድርጎታል።

ወደ ተጋጣሚ የጎል ክልል ደርሶ ግብ ማስቆጠር ላይም ባሕር ዳር ከተማ ደካማ የሚባል ሲኾን በኢትዮጵያ መድን በኩል ደግሞ የተሻለ እንደኾነ ከባለፉት የቅርብ ጊዜ ጨዋታዎቹ መገንዘብ ይቻላል፡፡

ባሕር ዳር ከተማ ከሦስት ጨዋታዎች ማስቆጠር የቻለው ሁለት ግቦችን ነው። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ መድኅን በተመሳሳይ ስድስት ጎሎችን በተጋጣሚው መረብ ላይ በማሳረፍ የተሻለ የሚባል ነው፡፡

ሁለቱ ክለቦች እስካሁን አራት ጊዜ የመገናኘት ዕድል ነበራቸው በዚህም አንድ አንድ ጊዜ ሲሸናነፉ ሁለት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥተዋል፡፡ ጨዋታቸውም ምሽት 12 ሰዓት ላይ ይካሄዳል፡፡

በ15ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምር ሊግ ሌላው የሚጠበቀው ጨዋታ በሀድያ ሆሳህና እና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል የሚካሄደው ነው፡፡ ጨዋታውም ዘጠኝ ሰዓት ይካሄዳል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here