የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ዛምቢያ ጨዋታ በኢትዮጵያዊያን ዳኞች ይመራል፡፡

0
294

ባሕር ዳር: ጥር 8/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኮትዲቯር አዘጋጅነት ከተጀመረ ዛሬ 5ኛ ቀኑን አስቆጥሯል፡፡

በውድድሩ ኢትዮጵያም በምስጉን ባለሙያዎቿ ተወክላ ጨዋታውን በአግባቡ እንዲካሄድ የበኩሏን ተሳትፎ እያበረከተች ትገኛለች፡፡

በአፍሪካ ዋንጫ የቴክኒክ ጥናት ቡድን ውስጥ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ተመድበው በመሥራት ላይ ናቸው፡፡

ኮሚሽነር ተስፋነሽ ወረታ ደግሞ በዳኞች ኮሚቴ አባልነት ተካትተው የቅድመ እና ድህረ ጨዋታዎችን በመገምገም የዳኝነት ሂደቱን በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡

ባምላክ ተሰማ ደግሞ በቀጥታ ጨዋታዎችን በዋና ዳኝነት ለመምራት ተሰይመዋል፡፡ እኝህ ቆፍጣና የመሐል ዳኛ ዛሬ ምሽት 5 ሰዓት በላውረንት ፖኩ ስታዲየም የሚደረገውን የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ዛምቢያ ጨዋታ ይመራሉ፡፡

በሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here