ባሕር ዳር: ጥር 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ በኳታር በተካሄደው የዶሃ ማራቶን ውድድር አትሌት እታለማሁ ስንታየሁ አሸንፋለች። አትሌት እታለማሁ ርቀቱን 2 ሰዓት 21 ደቂቃ ከ43 ሰከንድ በመጨረስ ነው ያሸነፈችው።
ሌሎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶችም እስከ አምስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል። በዚህ መሠረት ሙሉሃብት ጸጋ ሁለተኛ፣ ዝናህ ሰንበታ ሦስኛ፣ ሚነት አህመድ አራተኛ እንዲሁም ስንታየሁ ጥላሁን አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቀዋል።
በወንዶች የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ባለው ይሁኔ ሁለተኛ ኾኖ ሲያጠናቅቅ ምትኩ ጣፋ ሦስኛ፣ ድንቅዓም አየለ ደግሞ አራተኛ ደረጃን ይዟል፡፡
በወንዶች ምድብ ኬንያዊው አትሌት እዝራ ኪፕኬተር ታኑይ ውድድሩን 2 ሰዓት ከ7 ደቂቃ ከ28 ሰከንድ በመጨረስ ቀዳሚ መኾን ችሏል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!