ባሕርዳር: ጥር 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በ21ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምዬር ሊግ ሳውዝሀምፕተንን ያስተናገደው ማንቸስተር ዩናይትድ ከመመራት ተነስቶ ድል አድርጓል። በመጀመሪያው አጋማሽ ግብ የተቆጠረበት ማንቸስተር ዩናይትድ በሁለተኛው አጋማሽ ባስቆጠታቸው ግቦች ድል አድርጓል።
በሁለተኛው አጋማሽ ተጭኖ የተጫወተው ማንቸስተር ዩናይትድ በመጨረሻ ደቂቃዎች ግብ በማስቆጠር ነው ድል ያደረገው። ተስፈኛው ተጫዋች አማድ ዲያሎ በ82ኛው፣ 90ኛው እና 94ኛው ደቂቃ ያስቆጠራቸው ሦስት ግቦች ማንቸስተርን ባለ ድል አድርገዋል። አማድ ዲያሎ በጨዋታው ባሳየው ድንቅ ብቃት የጨዋታው ኮኮብ ተብሏል።
ማንቸስተር ዩናይትድ ድል ማድረጉን ተከትሎ በ26 ነጥብ ደረጃውን ወደ 12ኛ ከፍ አድርጓል። በሌላ የፕሪምዬር ሊጉ ጨዋታ ኢፕስዊች ታወን እና ብራይተን ያደረጉት ጨዋታ በብራይተን አሸናፊነት ተጠናቅቋል። ብራይተን በ31 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!