ባሕር ዳር: ጥር 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በ14ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ ቡና፣ ኢትዮጵያ መድን ከሐዋሳ ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። ፋሲል ከነማ እና ኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታው ቀን 9:00 ሰዓት ላይ ይደረጋል። ሁለቱ ቡድኖች አኹን ያላቸው ወቅታዊ አቋም ወጥ ያልኾነ ነው።
ክለቦቹ በደረጃ ሠንጠረዡ በ16 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ዘጠነኛ እና 10ኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኙት። ፋሲል ከነማ ያለፉትን ሦስት ተከታታይ ጨዋታዎች አንዱን አሸንፎ በሁለቱ አቻ ተለያይቷል።
ኢትዮጵያ ቡናም በተመሳሳይ ያለፉትን ሦስት ጨዋታዎች አንደኛውን አሸንፎ በሁለቱ አቻ ወጥቷል። ተመሳሳይ ነጥብ ያላቸው ሁለቱ ክለቦች የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ከዚህ በፊት 15 ጊዜ እርስ በእርስ ተገናኝተዋል። ስድስት ጊዜ ፋሲል ከነማ በማሸነፍ ቅድሚያውን ይወስዳል። ኢትዮጵያ ቡና ሦስት ጊዜ አሸንፏል። ቀሪው ስድስቱን ደግሞ አቻ የተለያዩበት ነው።
ምሽት 12:00 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድን ከ ሐዋሳ ከተማ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታም ተጠባቂ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!