ባሕር ዳር ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ጋር ይጫወታል።

0
130

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የ13ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየርሊግ ዛሬ ታኅሣሥ 30/2017 ዓ.ም ሲቀጥል ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ። በ19 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ ሦስተኛ ላይ የተቀመጠው ባሕርዳር ከተማ ከደረጃ ሠንጠረዡ ግርጌ አንድ ከፍ ብሎ የተቀመጠውን ሀዋሳ ከተማን ይገጥማል።

ባሕርዳር ከተማ በዚህ ጨዋታ ደረጃውን ለማሻሻል ወደ ሜዳ ይገባል። በሀዋሳ ከተማ በኩል ከወራጅ ቀጣና ስጋት ለመውጣት ጨዋታውን ማሸነፍ ይፈልጋል። ሀዋሳ ከተማ በ10 ነጥብ 17ኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው።

የሁለቱን ቡድኖች ወቅታዊ አቋም ስንመለከት ባለፉት ጊዜያት እርስ በእርስ ከአደረጓቸው አምስት ጨዋታዎች መካከል ሁለቱን ባሕርዳር ከተማ አንድ ጊዜ ደግሞ ሀዋሳ ከተማ ሲያሸንፍ ሁለት ጨዋታ ላይ ደግሞ አቻ ወጥተዋል።

ሁለቱ ቡድኖች በቅርቡ ከሌሎች ቡድኖች ጋር ያደረጉትን ጨዋታ ባሕርዳር ከተማ ሁለቱንም አቻ ሲለያይ ሀዋሳ ከተማ ደግሞ በአንዱ ሲሸነፍ ሌላውን ደግሞ አሸንፏል።
ጨዋታው 9:00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።

በዕለቱ ሁለተኛ መርሐ ግብር 12:00 ሰዓት ደሬዳዋ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት ጨዋታም ተጠባቂ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here