12ኛው የደሴ ከተማ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ።

0
193

ደሴ: ታኅሣሥ 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ)12ኛው የደሴ ከተማ አሥተዳደር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ “ስፖርት ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት በደሴ ከተማ ተካሂዷል።

አሚኮ ያነጋገራቸው ተሳታፊ ዑመር የሱፍ በሳምንት ስድስት ቀን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ 91 ኪሎ የነበረ ክብደታቸውን ዝቅ በማድረግ መቆጣጠር እንደቻሉ ነው የገለጹት፡፡

የአካል ብቃት አሠልጣኙ ሀብታም አሰፋን ጨምሮ ወይዘሮ ማህሌት ደርበው እና መምህር አብዱ የሱፍም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረጋቸው በርካታ ጥቅም አግኝተናል ብለዋል ፡፡

የደሴ ከተማ አሥተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ ሰይድ አራጋው 12ኛው የደሴ ከተማ አሥተዳደር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዋና ዓላማው ስፖርት ለሰላም ያለውን ፋይዳ ከፍ አድርጎ ማሳየት፣ ስፖርት ለአንድነት እና ለሰላም ያለውን ኀይል ለማስገንዘብ ያለመ ነው።

ኀላፊው ነዋሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባሕላቸው በማድረግ ከበሽታዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ለማስቻል ስፖርታዊ እንቅስቃሴው መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

የደሴ ከተማ ነዋሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የማድረግ ባሕል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ስለመምጣቱም ኀላፊው ተናግረዋል፡፡

“ስፖርት ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት የተካሄደው 12ኛው የደሴ ከተማ አሥተዳደር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከሕጻናት እስከ አረጋውያን ተሳትፈውበት በሰላም ተጠናቅቋል፡፡

ዘጋቢ፦ከድር አሊ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here