አዲስ አበባ: ታኅሣሥ 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕል ፌስቲቫል መክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ዳዊት ትርፉ ከ11ዱም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የባሕል ልዑካን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ዳዊት ትርፉ የባሕል ስፖርቶችን ለማልማት እና ለማሳደግ ከታች ከትምህርት ቤት ጀምሮ ሥራዎች እየተሠሩ መኾኑን ተናግረዋል።
15ኛው የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የባሕል ስፖርቶች ውድድር እና የባሕል ፌስቲቫል ከዛሬ ታኅሣሥ 26/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሚቀጥሉት 15 ቀናት ይካሄዳል።
በዚህ ውድድር የተመረጡ ስፖርተኞች በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ለሚካሄደው ሀገር አቀፍ የባሕል ስፖርቶች ውድድር እና የባሕል ፌስቲቫል ከተማ አሥተዳደሩን ይወክላሉ ነው የተባለው።
ዘጋቢ፦ ባዘዘው መኮንን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!