አርሰናል በፈረንጆቹ 2025 የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ድል ቀንቶታል።

0
273

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 23/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዛሬ በፈረንጆች 2025 የመጀመሪያ ቀን ሲሆን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ አርሰናል ከብሬንትፎርድ ጋር ተገናኝተዋል። በጨዋታውም አርሰናል 3 ለ 1 በኾነ ውጤት አሸንፏል።

በጨዋታው በመጀመሪያው አጋማሽ በ13ኛው ደቂቃ ላይ ቢ መብዩኖ ባስቆጠራት ጎል ብሬንትፎርዶች መምራት ችለው ነበር። ይሁን እንጅ አርሰናሎች ተጭነው በመጫወት ጋብሬል ጀሰስ በ29ኛው፣ ሜሪያኖ በ50ኛው ደቂቃ እና በጋብሬል ማርቲኔሊ በ53ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ጎሎች አማካኝነት ማሸነፍ ችለዋል።

አርሰናሎች ማሸነፋቸውን ተከትሎ ለዋንጫ የሚያደርጉትን ፉክክር አጠናክረዋል። ከመሪው ሊቨርፑል በስድስት ነጥብ ዝቅ ብለው ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጡም አስችሏቸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here