ባሕር ዳር: ታሕሣሥ 22/2017 ዓ.ም(አሚኮ) የ28 ዓመቱ የዌስትሃም ዩናይትዱ አንበል ጃሮድ ቦወን በሳለፋነው እሑድ ከመሪው ሊቨርፑል ጋር ጨዋታውን ሲያካሂድ ነው ጉዳት ያጋጠመው። ከጉዳት በኋላ በተደረገለት ምርመራ የግራ እግሩ ላይ የአጥንት ስብራት እንዳጋጠመው በግል የኢንስታግራም ገጹ ላይ መልዕክት እንዳስተላለፈ ቢቢሲ በስፓርት አምዱ አስነብቧል።
ቦወን በመልዕክቱ እግር ኳስ ላይ ጉዳት ያጋጥማል ወደ ቡድኔ በፍጥነት መመለስ ምኞቴ ነው ሲል ገልጿል። ተጨዋቹ በዚህ የውድድር ዘመን የዌስትሃም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው። አምስት ጎሎችን ሲያስቆጥር አራት ደግሞ አመቻችቶ አቀብሏል።
ክለቡ የመመለሻ ጊዜ ገደቡን ባያስቀምጥም የአንበሉ የጉዳት መጠን ግን ቀላል እንዳልሆነ ቢቢሲ አስነብቧል።
ዌስትሃም በመሪው ሊቨርፑል 5ለ0 መሸነፍ የሚታወስ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!