ባሕርዳር: ታኅሣሥ 22/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ዋይኒ ሩኒ ከፕለይማውንዝ ጋር ከሰባት ወራት በኋላ ተለያይተዋል። የ39 ዓመቱ የቀድሞ የእንግሊዝ አምበል ዋይኒ ሩኒ በክለቡ በነበረው ቆይታ 23 ጨዋታዎችን አድርጎ በአራቱ ብቻ ድል ሲቀናው በ13ቱ ደግሞ ተሸንፏል። በስድስት ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይቷል።
ዋይኒ ሩኒ በነበረው ቆይታም ውጤታማ ጊዜን ባለማሳለፉ ነው ክለቡን ለመልቀቅ የተገደደው። ሩኒ እሑድ ዕለት በኦክስፎርድ ዩናይትድ 2-0 መሸነፉን ተከትሎ አሠልጣኙ በዘጠኝ ጨዋታ ያለ ምንም ድል ባደረገው ጉዞ ከደጋፊዎች ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶበታል።
ሩኒ ከሽንፈቱ በኋላ የተሰነዘረውን ትችት እንደማይቀበለው ተናግሯል። ይህን ተከትሎ ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይቷል።
ዋይኒ ሩኒ ወደ አሠልጣኝነት ከመምጣቱ አስቀድሞ በተጫዋችነት ዘመኑ ለእንግሊዝ እና ለማንቸስተር ዩናይትድ በመጫዎት የጎል ሪከርዶች ባለቤት መኾን የቻለ ተጫዋችም ነበር።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!