እየወጡ ያሉ አዳዲስ ስፖርታዊ ጭምጭምታዎች።

0
229

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የ26 ዓመቱ የሊቨርፑል የቀኝ መስመር ተከላካይ ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ ለሪያል ማድሪድ ለመፈረም ተቃርቧል ተብሏል። እንግሊዛዊው ተጫዋች አሁን ያለው ኮንትራት በዚህ ክረምት እንደሚያልቅ ነው የስፔን ጋዜጦች ያስነበቡት። ሊቨርፑል አሌክሳንደር አርኖልድ ማድሪድን ከተቀላቀለ ኔዘርላንዳዊውን የባየር ሊቨርኩሰኑን ተከላካይ ጀርሚ ፍሪምፖንግ እና የባየር ሙኒክ ተከላካይን አልፎንሶ ዴቪስን ሊያስፈርም ይችላል ብሏል ቲምቶክ በዘገባው።

ማንቸስተር ሲቲ የ28 ዓመቱን የኖቲንግሃም ፎረስት የቀኝ መስመር ተከላካይ ኦላ አይናን በ34 ዓመቱ እንግሊዛዊ ካይል ዎከርን ለመተካት ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ዘሰን አስነብቧል። አርሰናል የ23 ዓመቱን የኢስፓኞል ግብ ጠባቂ ጆአን ጋርሺያን ለማስፈረም ይፈልጋል ሲል ሚረር አገኘውት ያለውን መረጃ ይዞ ወጥቷል።

የ39 ዓመቱ ፖርቹጋላዊ እና የአል ናስር አጥቂ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለማንቸስተር ሲቲ እንዲፈርም ሁለት ጊዜያት ጥያቄ ቢቀርብለትም የቀድሞ ክለቡ የማንቸስተር ዩናይትድ ተቀናቃኝ ኾኖ መጫዎት እንደማይፈልግ መግለጹን ቶክ ስፖርት አገኘውት ያለውን መረጃ ይዞ ወጥቷል። ቼልሲ እና ተቀናቃኙ ማንቸስተር ዩናይትድ ፈረንሳዊውን የፓሪስ ሴንት ዠርሜይን አጥቂ ራንዳል ኮሎ ሙኒን ለማስፈረም ፉክክር እያደረጉ መኾኑን ፉት መርካቶ አስነብቧል

ኒውካስትል ዩናይትድ የሌንስ መሐል ተከላካይን አብዱኮዲር ኩሳኖቭን በ25 ሚሊዮን ዩሮ ለማስፈረም ጥረት እያደረገ መኾኑ ሲዘገብ ተጫዋቹን የፕሪምየር ሊጉ ተቀናቃኞቹ ማንቸስተር ሲቲ፣ ቶተንሃም ሆትስፐር፣ ሌስተር ሲቲ እና ዎልቭስ የሚፈልጉት መኾኑ ፉክክር ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ ሲል ክሮኒክል የተሰኘ የዜና ገጽ ዘግቧል።

የ25 ዓመቱ የክሪስታል ፓላስ የግራ መስመር ተከላካይ ቲሪክ ሚቸል በላሊጋው አትሌቲኮ ማድሪድ እየተፈለገ መኾኑን ኮት አፍሳይድ አስነብቧል። ማንቸስተር ሲቲ ከሪያል ሶሴዳድ ወደ እንግሊዝ ለመዛወር ፍላጎት እንደሌለው የሚነገርለትን የ25 ዓመቱን ስፔናዊ አማካይ ማርቲን ዙቢሜንዲን የማስፈረም ፍላጎት ያለው ቢኾንም ዕድሉ ግን ጠባብ እንደኾነ ቲቢአር ፉትቦል ጽፏል።

ሳውዝሃምፕተን እና ኢፕስዊች የሬኔስን እና የፊንላንድን አማካኝ ግሌን ካማራን በጥር ወር ማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ነው ቲቢአር ፉትቦል አገኘውት ያለውን መረጃ ጠቅሶ የዘገበው። ሪያል ቤቲስ ብራዚላዊውን አማካኝ አርተርን ከጁቬንቱስ በውሰት ለመውሰድ ከተጫዋቹ ተወካዮች ጋር እየተነጋገሩ እንደሚገኙ ስፖርት ስፓኒሽ የተሰኘ ገጽ መዘገቡን ቢቢሲ በስፖርት ጭምጭምታ አምዱ ያስነበበው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here