የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የበዓል ሰሞን ጨዋታዎች ዛሬ ይጀምራሉ።

0
198

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 18ኛ ሳምንት የበዓል ጨዋታ ዛሬ ሲቀጥል በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ማንቸስተር ሲቲ ከኤቨርተን ተጠባቂ ጨዋታ ይጠብቀዋል። በዚህ ጨዋታ ማንቸስተር ሲቲ በውጤት ማጣት ቀውስ ወስጥ ይቀጥላል ወይስ ከውጤት ቀውስ ይወጣል የሚለው ይጠበቃል፡፡

አሠልጣኙ ፔፕ ጋርዲዮላ የዛሬውን ጨዋታ አሸንፎ ለመውጣት የሚያደርጉት አሠላለፍ ይጠበቃል፡፡ ማንቸስተር ሲቲ ሁለት ተጨዋቾቹ በጉዳት የማይሰለፉ ሲኾን በኤቨርተን በኩልም ሁለት የቡድኑ አባላት በስብስቡ ውስጥ አይካተቱም፡፡ ለሦስት ተከታታይ ጊዜ ሽንፈትን ያስተናገደው ማንቸስተር ሲቲ በተከታታይ ጊዜ አቻ የወጣውን እና አንድ ጊዜ ማሸነፍ የቻለው ኤቨርተንን በሜዳው ጋብዞ 9፡30 ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ሁለቱ ቡድኖች 194 ጊዜ ሲገናኙ 80 ጊዜ ማንቸስተር ሲቲ ሲያሸንፍ 66 ጊዜ ኤቨርተን አሸንፏል። 48 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል፡፡ ዛሬ ሌሎች ተጠባቂ ጨዋታዎችም 12፡00 ሰዓት ይቀጥላሉ። በርን ማውዝ ከክርስታል ፓላስ፣ ቼልሲ ከፉልሃም፣ ኒውካስትል ከአስቶንቪላ፣ ኖቲንግሀም ፎረስት ከቶትንሀም ሆትስፐር እና ሳውዛምፕተን ከዌስትሃም ይጫወታሉ።

ዎልቭስ ከማንቸስተር ዩናይትድ ምሽት 2፡ 30 ሲካሄድ ሊቨርፑል ከሌስተር ጋር ምሽት 5 ሰዓት የሚያደርጉትም ሌላው የዛሬ ምሽት መርሐ ግብር ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here