የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሱዳን አቻው ጋር ሁለተኛውን የደርሶ መልስ ጨዋታ ነገ ያደርጋል፡፡

0
117

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ እግር ኳስ መሥራቾቹ ኢትዮጵያ እና ሱዳን በቻን ውድድር ተሳታፊ ለመኾን የደርሶ መልስ ሁለተኛ ጨዋታቸውን ነገ ያደርጋሉ።

ለቻን የመጨረሻ ማጣርያ ከሱዳን ብሔራዊ ቡድን ጋር ሁለተኛውን የደርሶ መልስ ጨዋታ የሚያደርጉት ዋልያቹ በሊቢያ ቤንጋዚ ነው የሚያካሂዱት።

የመጀመሪያውን ጨዋታ 2ለ0 የተረታችው ኢትዮጵያ በመልሱ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ይጠበቅባታል፡፡

ኢትዮጵያ እና ሱዳን ይሄኛውን ዙር ሳይጨምር 25 ጊዜ ሲገናኙ 8 ጊዜ ኢትዮጵያ 9 ጊዜ ሱዳን ስታሸንፍ 8 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።

ጨዋታው ነገ ታኅሣሥ 16/2017 ዓም 11:00 ሰዓት ይካሄዳል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here