ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ፈረንሳያዊ የፊት መስመር ተጫዋች ባርሴሎናን ሊቀላቀል ይችላል። ቼልሲ ክሪስቶፎር ንኩንኩን ለባርሴሎና ለዝውውረ አቅርቦታልም ተብሏል።
የማንቸስተር ዩናይትዱ ፖርቹጋላዊ አሠልጣኝ ሩበን አሞሪም የ27 ዓመቱን እንግሊዛዊ አጥቂ ማርከስ ራሽፎርድን በክለባቸው እንዲያቆዩት ጫና የማይደረግባቸው ቢኾንም ተጫዋቹ በተደጋጋሚ አለመገኘቱ በጥሩ የዝውውር ጊዜ አሳልፈው ሊሰጡት እንደሚችሉ ነው መረጃዎች የሚያሳዩት።
ባየር ሙኒክ የ20 ዓመቱን እንግሊዛዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች ጄሚ ጊተንስን ለማስፈረም ማሰቡን መረጃዎች እየወጡ ነው። አርሰናል የአታላንታውን የ25 ዓመት ጣሊያናዊ የፊት መስመር ተጫዋች ማቲዎ ሬቴጊን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምሯል።
በኤሲ ሚላኑ አሠልጣኝ ፓውሎ ፎንሴካ እና በፈረንሳዩ ተከላካይ ቴዎ ሄርናንዴዝ መካከል ያለው ውጥረት የግራ ተመላላሹን ከሳንሲሮ እንዲወጣ ምክንያት ሊኾን ይችላል ተብሏል። ሪያል ማድሪድ እና ማንቸስተር ዩናይትድ ለተጫዋቹ ፍላጎት እንዳላቸው እየተዘገበ ነው።
በሌላ በኩል ቶተንሃሞች የ26 ዓመቱን የአታላንታ ተከላካይ ቤን ጎፍሬይን በአጭር ጊዜ የውሰት ውል ለማስፈረም መቃረባቸው እየተነገረ ነው።
የ27 ዓመቱ የሊቨርፑል አጥቂ ሉዊስ ዲያዝ በአንፊልድ ደስተኛ በመኾኑ ክለቡን የመልቀቅ ዕቅድ እንደሌለው ቢቢሲ በስፖርት ጭምጭምታ ገጹ አስፍሯል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!