ባሕር ዳር: ታኅሳስ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአርሰናሉ የክንፍ አጥቂ ቡካዮ ሳካ በጉዳት ምክንያት ለሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ አሠልጣኙ ሚኬል አርቴታ አስታውቀዋል፡፡ ሳካ አርሰናል ክርስቲያል ፓላስን 5 ለ 1 ባሸነፈበት ጨዋታ በጉዳት ምክንያት ጨዋታውን አቋርጦ መውጣቱ ይታወሳል፡፡ የተጫዋቹ ጉዳት ለምን ያክል ጊዜ ከሜዳ ያርቀዋል የሚለው ጉዳይ በሕክምና ቡድኑ ምርመራ ሲደረግበት ቆይቷል፡፡
ከቀናት በኋላ የአርሰናሉ አሠልጣኝ ሚኬል አርቴታ ሳካ ለሳምንታት ከጨዋታ ውጭ መኾኑን ይፋ አድርገዋል፡፡
የ23 ዓመቱ እንግሊዛዊ ኮኮብ ቡካዮ ሳካ በውድድር ዓመቱ በሁሉም ውድድሮች ባደረጋቸው 24 ጨዋታዎች ዘጠኝ ግቦችን አስቆጥሮ 13 ለግብ የሚኾኑ ኳሶችን ማቀበሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የገጠመው ጉዳት ከበድ ያለ መኾኑን የገለጹት አሠልጣኝ አርቴታ ተጨዋቹ በፍጥነት ወደ ሜዳ እንደሚመለስ የሚቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ አመላክተዋል፡፡
ሳካ በገጠመው ጉዳት ስሜታዊ መኾኑንም አንስተዋል፡፡ ከቡካዮ ሳካ በተጨማሪ ራህም ስተርሊንግም መጎዳቱን አሠልጣኙ መግለጻቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!