ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ማንቸስተር ዩናይትዶች ኤደርሰንን ለማስፈረም ትልቅ ፍላጎት እንዳላቸው ተሰምቷል። ብራዚላዊው የመሐል አማካይ ቦታ ከፍተኛ ትኩረት ከሚሰጣቸው ተጫዋቾች መካከል አንዱ እንደኾነ ነው እየተገለጸ የሚገኘው። አሁን ለአታላንታ እየተጫወተ ነው።
የ20 ዓመቱን የአየርላንድ ሪፐብሊክ የፊት መስመር ተጫዋች ኢቫን ፈርጉሰን ከብራይተን ለመውሰድ ዌስትሃም ከሌስተር ሲቲ እና ሳውዝአምፕተን ጋር በፉክክር ውስጥ መግባቱ ተሰምቷል። ሳውዝሃምፕተን ከፕሪምየር ሊጉ የሚወርድ ከኾነ የ18 ዓመቱን ታይለር ዲቢሊንግን ሊሸጥ ይችላል ተብሏል።
ማንቸስተር ዩናይትድ እና ኒውካስል ለእንግሊዛዊው አማካይ ፍላጎት ያሳዩ ክለቦች መኾናቸውን ቢቢሲ ከኢንሳይደር አገኘውት ያለውን መረጃ ጠቅሶ ጽፏል።ዌስትሃም፣ ፉልሃም እና ክሪስታል ፓላስ የጁቬንቱሱን አማካይ ኒኮሎ ፋጊዮሊን ለማስፈረም ፍላጎት ቢያሳዩም የ23 ዓመቱ ጣሊያናዊ ኢንተርናሽናል ተጫዋች ፍላጎቱ ወደ ቶተንሃም እንደኾነ ቱቶ ስፖርት አስነብቧል።
ሊቨርፑል እና ፓሪስ ሴንት ዠርሜይን የሊዮኑን ፈረንሳዊ አማካይ ራያን ቼርኪን ለማስፈረም ጥረት እያደረጉ መኾናቸው ነው የተነገረው። ቼልሲዎች የአርቢ ሊፕዚንጉን እና የስሎቬኒያ የፊት አጥቂ ቤንጃሚን ሴስኮን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል ነው የተባለው። በሌላ በኩል አርሰናል ሴስኮን ለማስፈረም ንግግር ማድረጉ እና ተጫዋቹ ከተወካዮቹ ጋር ጥሩ ግንኙነት መፍጠራቸው ነው እየተነገረ ያለው።
ኤሲ ሚላን የኤቨርተኑን የ27 ዓመቱን እንግሊዛዊ አጥቂ ዶሚኒክ ካልቨርት ሌዊን በቀጣዩ ክረምት ለማዛወር ፍላጎት እንዳሳዩ እየተዘገበ ነው። ቫሌንሺያ፣ ሪያል ቤቲስ እና ቪያሪያል የ28 ዓመቱን ብራዚላዊ አማካይ አርተር ሜሎን ማስፈረም እንደሚፈልጉ መገለጹን ቢቢሲ በስፖርት የጭምጭምታ አምዱ አስነብቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!