የአፍሪካ እግር ኳስ ማኅበር የ2024 የዓመቱ ምርጦችን አሳውቋል።

0
192

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ እግር ኳስ ማኅበር የ2024 የዓመቱ ምርጦችን ሲያሳውቅ ናይጀሪያዊ የአትላንታ ተጫዋች ሉክማን የዓመቱ የአፍሪካ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል። የኮቲዲቯሩ ሲሞን አዲንግራ፣ የጊኒው ሰሪሆ ጉረሲ፣ የሞሮኮው አሽራፍ ሀኪሚ እና የደቡብ አፍሪካው ሩንዊን ዊልያምስ የሉክማን ተፎካካሪዎች ነበሩ። ነገር ግን በዓመቱ ድንቅ አቋም የነበረው ሉክማን አሸናፊ ኾኗል።

ተጫዋቹ ክለቡ አታላንታ ባለው ዓመት የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ሲያነሳ ድንቅ እንቅስቃሴ ነበረው። ከባየርሊቨርኩሰን ጋር በነበረው የፍጻሜ ጨዋታ ናይጀሪያዊው ኮከብ ሦስት ግቦችን ማስቆጠሩም ይታወሳል። በአፍሪካ ዋንጫ ናይጀሪያ ፍጻሜ ድረስ ስትጓዝ ሉክማን ሚናው ጥሩ ነበር። የውድድሩ ምርጥ ቡድን ውስጥም መካተት ችሏል።

በተጨማሪም በሴቶች ዘርፍ የዛምቢዋ ባርባራ ባንዳ የዓመቱ ምርጥ ተብላለች። የዓመቱ ምርጥ አሠልጣኝ በወንዶች ዘርፍ የኮትዲቯሩ አሠልጣኝ ኢምርስ ፋየ ኾኗል። የቲፒ ማዜንቤ የሴቶች ክለብ አሠልጣኝ ላሚያ ቡማህዲ የሴቶች ምርጥ አሠልጣኝ ተብላ ተመርጣለች። በሞሮኮ ማራካሽ በተካሄደው መርሐ ግብር እነዚህ እና ሌሎች ሽልማቶችም ተከናውነዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here