የፕርሚየር ሊጉ ዳኛ ዴቪድ ኩት ከሥራቸው ተሰናበቱ።

0
154

ባሕር ዳር: ታኅሣሥ 1/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዳኛ የነበሩት ዴቪድ ኩት ከሥራቸው መሰናበታቸውን የፕርሚየር ሊጉ ፕሮፌሽናል ዳኞች ማኅበር አስታውቋል።

ዋና ዳኛው በቅርቡ በተሰራጨ የቪዲዮ ቅጂ ሊቨርፑልን እና የቀድሞ አሠልጣኛቸውን የርገን ክሎፕን ሲሳደቡ እና ሲተቹ በተሰራጨው የቪዲዮ መረጃ ተስተውለዋል።

ይህን የቪዲዮ መረጃ ተከትሎ የ49 ዓመቱ ዳኛ ዴቪድ ኩት ከሥራቸው ታግደው ምርመራ ሲደረግባቸውም ቆይቷል።

የምርመራ ውጤቱም ዳኛው ጥፋተኛ መኾናቸውን አረጋግጧል።

በዚህም መሠረት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ዳኛ ዴቪድ ኩት ተሰናብተዋል። ከዚህ በኋላም በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች እንደማንመለከታቸው ቢቢሲ በስፖርት ገጹ አስነብቧል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here