ባሕር ዳር: ኅዳር 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ሀገራዊ የስፖርት ልማት ስብራቶቻችንን በሳይንሳዊ ጥናት እንፈታለን” በሚል መሪ መልዕክት ሀገራዊ ምክክር እየተካሄደ ነው። ምክክሩን የባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ነው፡፡ ምክክሩ እንደ ሀገር በስፖርት ልማት ያሉ ስብራቶችን በጥናት በመለየት እና መፍትሄ ለማስቀመጥ ዓላማ ያደረገ ነው፡፡
የስፖርት ኢንዱስትሪውን በማዘመን ኢትዮጵያ ከዘርፉ ተጠቃሚ የምትኾንበትን መንገድ መቀየስ የሚያስፈልግ መኾኑኑም ተመላክቷል፡፡ በምክክሩ ላይ የተገኙት የባሕል እና ስፖርት ሚኒስትሯ ሸዊት ሻንካ ስፖርት ከጨዋታነት ባሻገር በአንድ ሀገር ሕዝቦች መካከል አንድነትን፣ መከባበር እና የመደመር መንፈስን በማጎልበት ማኅበራዊ ትስስርን የመፍጠር ኃይል አለው ብለዋል፡፡
ለዜጎች የሥራ እድል በመፍጠር እና ገቢን በማመንጨት ለሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዳለውም ተናግረዋል፡፡ በዓለም አቀፍ መድረኮች በስፖርታዊ ውድደሮች በሚመዘገቡ ድሎች እና ተሳትፎዎች የሀገርን ገጽታ በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለውም ገልጸዋል፡፡
መንግሥታዊ አካላት፣ ሕዝባዊ የስፖርት ማኅበራት መሪዎች እና ባለድርሻ አካላት ለኢትዮጵያ የስፖርት ልማት በኃኀላፊነት መንፈስ እንዲሠሩም አሳስበዋል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!