የመርሲሳይድ ደርቢ ጨዋታ ተራዘመ።

0
200

ባሕር ዳር: ኅዳር 28/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በጉዲሰን ፓርክ ስታዲየም ሊካሄድ የነበረው የኤቨርተን እና ሊቨርፑል የመርሲሳይድ ደርቢ ጨዋታ ለሌላ ጊዜ መራዘሙን ዘ አትሌቲክ አረጋግጧል። የመርሲሳይድ ደርቢ የተራዘመው በእንግሊዝ ሊቨርፑል ከተማ ባለው አስቸጋሪ የአየር ንብረት ምክንያት መኾኑ ተገልጿል።

በአካባቢው የተከሰተው አውሎ ንፋስ ለደህንነት አስጊ በመኾኑ በአካባቢው ባለስልጣናት ለደህንነት ሲባል ጨዋታው እንዳይደረግ መወሰኑ ተነግሯል።

ጉዲሰን ፓርክ ስታዲየም የመጨረሻውን የመርሲሳይድ ደርቢ ጨዋታ ለማድረግ ተዘጋጅቶ እንደነበር ይታወቃል።

በሌላ የዛሬ መርሐ ግብር 11:30 ሰዓት ባየር ሙኒክ ከሄደንሄም፤ 12:00 ሰዓት ላይ ክሪስታል ፓላስ ከማንችስተር ሲቲ፣ አስቶን ቪላ ከሳውዝሀምፕተን እና ብሬንትፎርድ ከኒውካስል ይገናኛሉ።

12:15 ሰዓት ሪያል ቤቲስ ከባርሴሎና፤ 2:00 ሰዓት ላይ ጁቬንቱስ ከቦሎኛ፤ 2:30 ሰዓት ማንችስተር ዩናይትድ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። ምሽት 5:00 ሰዓት ላይ ደግሞ ጂሮና ከሪያል ማድሪድ ይጫዎታሉ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here