በእግር ኳስ ህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀይ ካርድ የተመለከተው ማኑአል ኑዌር ።

0
195

ባሕር ዳር: ኅዳር 25/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጀርመናዊ ማኑኤል ኑዌር በባየር ሙኒክ እና በጀርመን ብሔራዊ ቡድን በድንቅ ግብ ተጠባቂነት እያገለገለ ነው። በክለብ ደረጃ የሻምፒዮንስ ሊግን ጨምሮ፣ የቦንደስ ሊጋ እና የጀርመን ዋንጫን ጨምሮ ትልልቅ ድሎችን አሳክቷል።

ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን ጋርም በዓለም ዋንጫን እና በአውሮፓ ደምቋል። በእነዚህ ሁሉ ክብሮቹ መሀል በጥሩ ሥነ ምግባር የሚታወቀው ኑዌር ትናንት ምሽት ቀይ ካርድ ተመልክቷል።

ባየር ሙኒክ ከባየር ሊቨርኩሰን ጋር ትናንት በጀርመን ዋንጫ ሲጫወት ነው ኑዌር በካርድ ከሜዳ ወጥቷል። ጨዋታውን ሊቨርኩሰን ሙኒክን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ኑዌር ገና በ17ተኛው ደቂቃ በሊቨርኩሰኑ ፍሪንፖግ ላይ በሠራው ጥፍት በቀይ ወጥቷል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here