ባሕር ዳር: ኅዳር 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ)
የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 10ኛ ሳምንቱ ላይ ደርሷል። ዛሬ የ10ኛ ሳምንት ሁለት ጨዋታዎች ይከናወናሉ። 10 ሰዓት ድሬዳዋ ከሲዳማ ቡና ምሽት 1ሰዓት ደግሞ መቻል ከቅዱስ ጊዮርጊስ ይጫወታሉ።
ጨዋታዎችን በሜዳው እያከናወነ ያለው ድሬዳዋ ከተማ በ12 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኘው። ተጋጣሚው ሲዳማ ቡና ደግሞ በ13 ነጥብ ስደስተኛ ላይ ይገኛል።
ሲዳማ ቡናዎች አጀማመራቸው ጠንካራ ነበር። ነገር ግን በተከታታይ ሦስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም። ባለፈው ጨዋታ በፋሲል ከነማ መሸነፋቸውም ይታወሳል።
ምሽት አንድ ሰዓት የሚጀመረው የቅዱስ ጊዮርጊስ እና መቻል ጨዋታ ጥሩ ፉክክር እንደሚታይበት ተጠብቋል።
ፈረሰኞቹ በሰባት ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ናቸው። መቻሎች ደግሞ ሊጉን እየመሩ ነው። 17 ነጥብ ሰብስበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!