በእንግሊዝ የፕሪምየር ሊግ ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ።

0
179

ባሕር ዳር: ኅዳር 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ)

የ14ተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጀምራል።

ኢፕሲዎች ከክርስቲያል ፓላስ እና ሌስተር ከዌስትሃም የዛሬ መርሐ ግብሮች ናቸው።

አዲስ አዳጊው ኢፕሲዎች በ13 የሊጉ ጨዋታዎች ዘጠኝ ነጥቦችን አግኝቷል። በደረጃ ሰንጠረዡም ሳውዝ አፕተንን ብቻ በልጦ 19ኛ ላይ ይገኛል። ተጋጣሚው ፓላስም በተመሳሳይ ነጥብ በግብ ክፍያ ተሽሎ 17ተኛ ላይ ነው የተቀመጠው።

የዛሬው ጨዋታም ከወራጅ ቀጠናው ለመውጣት የሚደረግ ብርቱ ፉክክር ይኾናል።

ሩድ ቫኒስትሮይ ሌስተርን እየመራ በሚያካሂደው የመጀመሪያ ግጥሚያ በጥንካሬው ላይ የማይገኘው ዌስትሃምን ይጋብዛል።

ሌስተር ሲቲ በ10 ነጥቦች 16ኛ ደረጃ ላይ ኾኖ ጨዋታውን ያደርጋል። ተጋጣሚው ዌስትሃም ደግሞ በአምስት ነጥብ ተሽሎ 14ኛ ላይ ነው።

የ14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገም ሲቀጥሉ አርሰናል በሜዳው ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here