በሦስተኛ ዙር ኤፍኤ ካፕ ማንቸስተር ዩናይትድ ከአርሰናል ይገናኛሉ።

0
145

ባሕር ዳር: ኅዳር 24/2017 ዓ.ም (አሚኮ)

የሦስተኛ ዙር የእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ የእጣ ድልድል ይፋ ኾኗል። በዕጣው መሰረት

ማንቸስተር ዩናይትድ እና አርሰናል እርስ በእርስ ይገናኛሉ።

ጨዋታውም ከወዲሁ ትልቅ ትኩረት ያገኘ ኾኗል። ማንቸስተር ዩናይትድ ያለፈው ዓመት የኤፍኤ ካፕ አሸናፊ ነበር።

በተመሳሳይ ሊቨርፑል ከአግሪንግተን፣ ማንቸስተር ሲቲ ከሳልፎርድ ሲቲ፣ ቶትንሃም ከታምወርዝ፣ ኒውካስትል ከብሮምሊ፣ ፍልሃም ከብሬንት ፎርድ፣ አስቶን ቪላ ከዌስትሃም ከመርሐ ግብሮቹ መካከል ናቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here