ባሕር ዳር: ኅዳር 20/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በድሬዳዋ ስታድየም እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዘጠንኛ ሳምንት ላይ ደርሷል።
በቀን ሁለት ጨዋታዎችን እያካሄደ የሚገኘው ፕሪምየር ሊጉ ዛሬም ጨዋታዎችን ያካሂዳል። አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ደግሞ ቀዳሚው ጨዋታ ነው። ጨዋታው ቀን 10:00 ላይ ይካሂዳል።
የእለቱ ሁለተኛ ጨዋታ ደግሞ አርባምንጭ ከተማን ከመቻል ያገናኛል። ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሸር ካምፓኒ የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ጨዋታው ምሽት 1:00 ላይ ይካሄዳል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!