ባሕር ዳር: ኅዳር 19/2017 ዓ.ም (አሚኮ)
የፕሪምየር ሊጉ ክለብ ሌስተር ሲቲ ሩድ ቫኒስተሮይን አዲስ አሠልጣኝ ለማድረግ ተቃርቧል።
በአሠልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በዚህ ዓመት ወደ ፕሪምየር ሊጉ ያደገው ሌስተር ማሬስካን በቼልሲ መነጠቁ ይታወሳል። በምትካቸው ስቲቭ ኩፐርን መሾሙም ይታወሳል።
ነገር ግን ክለቡ ውጤታማ ጉዞን እያደረገ አይደለም። በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊጉ 16ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሌስተር ባለፈው ሳምንት አሠልጣኙ ኩፐርን ማሰናበቱ ይታወሳል።
ቢቢሲ በስፖርት ገጹ ላይ ሌስተር ሲቲ ቫኒስትሮይን ለመቅጠር መስማማቱን ጽፏል።
ቫኒስትሮይ በዩናይትድ ቤት የቴን ሃግ ምክትል ነበር። ቴንሃግ ከተሰናበተ በኋላ በጊዜያዊ የአሠልጣኝነት ጊዜው በዩናይትድ ቤት የፈጠረው የቡድን አሸናፊነት ስሜት በሌሎች ክለቦች ተፈላጊ እንዲኾን አድርጎታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!