የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ዛሬም ይቀጥላሉ።

0
208

ባሕር ዳር: ኅዳር 18/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ አምስተኛ ጨዋታዎች ትናንት መካሄድ ጀምረዋል። ዛሬ ዘጠኝ ጨዋታዎች ይካሄዳሉ። ከዛሬ መርሐ ግብሮች መካከል ሊቨርፑል ሪያል ማድሪድን በሜዳው የሚያስተናግድበት ጨዋታ የተለየ ትኩረት አግኝቷል።

ሊቨርፑል በዚህ ዓመት ያደረጋቸውን አራት የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች በሙሉ አሸንፏል። በፕሪምየር ሊጉም ከተከታዩ ማንቸስተር ሲቲ በስምንት ነጥብ በልጦ የሊጉ አናት ላይ ተቀምጧል።

ሪያል ማድሪድ በሻምፒዮንስ ሊጉ የሊቨርፑልን ያህል ዘንድሮ ጠንካራ አይደለም። በአራት ጨዋታዎች ስድስት ነጥቦች ብቻ ሠብሥቧል። በላሊጋውም ቢኾን አጀማመሩ በተጠበቀው ልክ ኾኖ አልተገኘም።

ሪያል ማድሪድ በሊቨርፑል ላይ የ2018ቱን የፍጻሜ ጨዋታ ጨምሮ ሊቨርፑል ላይ ተደጋጋሚ የበላይነት ወስዷል።

በዛሬው ጨዋታ የሊቨርፑል የተሻለ ብቃት ላይ መገኘት እና የሪያል ማድሪድ በተጫዋቾች ጉዳት መፈተን ለሊቨርፑል መልካም አጋጣሚ ሊኾን እንደሚችል ቢቢሲ በስፖርት ገጹ አስነብቧል።

በሌሎች ጨዋታዎች አስቶን ቪላ ከጁቬንቱስ፣ ሞናኮ ከቤኔፊካ፣ ዳይናሞ ዛግሬብ ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ፣ ፒኤስቪ ከሻካታር ዶኔስክ ይጫወታሉ።

ሴልቲክ ከክለብ ብራግ፣ ቦሎኛ ከሊል፣ ስቱርም ከጅሮና እና ሬድስታር ከስቱት ጋርት የሚያደርጓቸው ጨዋታዎችም የዛሬ መርሐ ግብሮች ናቸው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here