የማንቸስተር ሲቲ የቁልቁለት ጉዞ!

0
184

ባሕር ዳር: ኅዳር 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የማንቸስተር ሲቲው አሠልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በቶተንሃም 4 ለ 0 ሽንፈት ከደረሰባቸው በኋላ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ዕውነታውን መቀበል አለብን የሚሉት አሠልጣኙ ይህን ዕውነት ካልተቀበልን ለቀጣዩ መሻሻል አንችልም ብለዋል። አሠልጣኙ አሁን የገጠማቸውን ዱብዳ ነገር ማስተካከል እንዳለባቸውም ነው የተናገሩት፡፡

ከጨዋታው በኋላ ለቢቢሲ ምንም የምና ገረው ነገር የለም ካሉ በኃላ ስፐርሶችን ከሜዳው ውጪ ሲቲን ስላሸነፉ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።

በተከታታይ ሽንፈትን እያስተናገዱ ያሉት አሠልጣኙ አሁንም ግን በተጫዋቾቹ ላይ ያላቸው ዕምነት የማይቀየር መኾኑን አንስተዋል።

አምስት ተከታታይ ሽንፈቶችን ሲያስተናግዱ አሁንም አቋማቸው ያው አልተናወጠም ይህም ሌላው የሰውየው ልዩ ባሕሪ ተደርጎ ተወስዷል፡፡

ፔፕ ጋርዲዮላ በአሠልጣኝነት እና ሲቲ እንደ ክለብ አጋጥሞት የማያውቀውን ነገር የገጠመው ሲኾን ይህም ለመጨረሻ ጊዜ በ2006 ስቱዋርት ፒርስ በነበሩበት ወቅት ከገጠማቸው ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የገጠማቸው የቁልቁለት ጉዞ ኾኗል።

ሊቨርፑል ዛሬ ከሳውዝአምፕተን ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ የሚያሸንፍ ከኾነ ሁለተኛ ደረጃ የተቀመጡት ሲቲዎችን በስምንት ነጥብ ይርቃቸዋል፡፡

በቀጣይም ሲቲ በአንፊልድ ከደረጃ ሰንጠረዡ መሪ ሊቨርፑል የሚገናኝ ይኾናል።

በስምንት ዓመታት ውስጥ እንደዚህ አይነት ነገር ገጥሟቸው የማያውቁት ፔፕ ጋርዲዮላ “ሦሥት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን በተከታታይ እንሸነፋለን ብዬ አላስብም ነበር፤ ነገርግን በሚያስደንቅ ኹኔታ ደጋግመን ተሸንፈናል” ሲሉ መራር ሽንፈታቸውን ገልጸዋል።

አንዳንድ ጊዜ ዕውነታውን መካድ አንችልም ሲሉ መግለጻቸው ሽንፈቱ እንዳመማቸው ማሳያ ነው፡፡ በእግር ኳስ ውስጥ ይከሰታል ሲሉም ተጫዋቾችን አጽናንተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here