ባሕር ዳር: ኅዳር 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በ2025 የሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ጋር ይጫወታል።
ዋሊያዎቹ ከምድብ ስምንት አንድ ነጥብ ብቻ ሰብስበው የሞሮኮው ድግስ ላይ እንደማይገኙ ተረጋግጧል።
በአንጻሩ የዲሞክራቲክ ኮንጎ ብሔራዊ ቡድን 13 ነጥብ በማግኘት 2025ቱ የአፍሪካ ዋንጫ አልፏል።
ጨዋታው ከምሽቱ 1:00 ላይ ይከናወናል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!